Sunday, February 20, 2011

በአጋጣሚው ሁሉ ብንነጋገር

ማለዳ ነው ከአዲስ አበባ የእረፍት ጊዜዬን  ቤተሰቦቼ ጋር አሳልፌ ወደምማርበት ባሕርዳር ከተማ   ለማቅናት መስቀል አደባባይ ባስ ለመያዝ  ያመራሁት፡፡ በጠዋት ብነሳም እንኳን መንገድ ላይ ታክሲ አጥቼ ስለነበር  ቲኬት የቆረጥኩበት ባስ  አመለጠኝ አላመለጠኝ የሚል ሀሳብ ሲመላለስብኝ  ጥቂት የማይባል ጊዜያትን አሳለፍኩ፡፡ ይሁን እንጂ በአጋጣሚ  አንዲት ታክሲ ከስድስት ኪሎ አከባቢ ስመጣችልኝ ወደ ውስጧ ዘልቄ ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡ እንደፈራሁት አልነበረም  ባሱ አልተንቀሳቀሰም፡፡ ለጊዜው መንፈሴ ተረጋጋ ይሁን እንጂ ቀጥል አድርጎ  በውስጤ ሌላ ሀሳብ በተራው ተተካ ፤ ባሱ ውስጥ ከጎኔ መቀመጫ ላይ የሚቀመጠው  ሰው ማንነት! ለምን አትበሉኝ መንገዱ ረጅም ስለሆነ  አብሮኝ የሚሆነው ሰው ወይንም በስርዓት ልንወያይ የሚችል  አሊያም ደግሞ የያዝኳቸውን መንፈሳዊ መጻህፍት እንዳላነብ  እንቅፋት ባይሆንብኝ ስለምመርጥ ነበር፡፡ ባሱ ውስጥ እንደገባሁ  የወንበር ቁጥሬን እና የቲኬት ቁጥሬን አነጻፀርኩ ፡፡ ፊት ለፊቴ ላይ አገኘሁት ፤የእኔ ወንበር ክፍት ሲሆን  ከጎን በእድሜ የገፉ አረጋዊ ተቀምጠዋል፡፡ መውጫው ሰዓት ደረሰና ባሱ መንገዱን ቀጠለ፡ ብዙ ተጓዝን  ሁላችንም ጠዋት ያጣናትን እንቅልፍ ለማካካስ ይመስላል ወነበራችን ላይ ደገፍ ደገፍ ብለን አሸለብን፡፡ ብዙ ሰዓታት አለፉ በሳችንም መገሰገሱን ተያያዘው፡፡ ይሁን እንጂ እኔ እና አዛውንቱ እስካሁን ቃልም አልተለዋወጥን፡፡ ምን ላድርግ የጋራ አጀንዳ አጣሁ፡፡ መጻህፈቶቼን እንዳላወጣ ቦርሳዬ እሩቅ ነው፤ በአጋጣሚ መንገድ ስንቆም ካላወጣሁት በስተቀር፡፡ እንደምንም ብዬ  አባይ በረሀ ስንደርስ የተፈጥሮውን ውበት አና የፈጣሪን ድንቅ አሰራር በመመልከት  የሆነ ቃል በመሰንዘር ዝምታውን ሰበርኩ፡፡ ትንሽ እነዳወሩኝ  አዲሱን መንገድ እና በጣሊያን የተሰራውን ድልድይ በማነፃፀር  በዚህ ነበር በዚያ ነበር እያሉኝ አቅጣጫ ያሳዩኝ  ጀመር፡፡ እኔም ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ቃላቶች ተመላለስን፡፡ ቀጠል አድርገው ዋይ አስካሁን ጣሊያን ቢገዛን ኖሮ ምን ያህል አድገን  ነበር አሉኝ፡፡ እንደዚህ አይነት አባባል አጥብቄ የምጠላው ስለነበር ትዕግስቴን ተፈታተነኝ፡፡ ትክክል እንዳደለ እና ብዙ ነገሮችን እንዳጣን ፤ ለዚህም አብዛኛውን የአፍሪካ ሀገራት ለዘመናት ያህል በቀኝ ግዛት ውስጥ ኖረው ምንም እንዳልተፈየዱ በማስረጃነት ለማቅረብ ሞከርኩ፡፡ በዙ ከተከራከሩኝ በኃላ  አጀንዳውን ትንሽ ዞር አድርገው የተማረው አካል በሀገሩ እንዲሰደድ ዋነኛ ምክንያቱ የመንግስት አስተዳደር ነው፡፡ ሀገሪቱ ምንም ተስፋ የላትም፤ መቼም አታድግ ፤ ሁሉ ጥሏት እየሄደ እንደኛ አይነቱ ሰው ብቻ ቀራት እያሉ ምሬታቸውን እና የውስጥ ብሶታቸውን ተነፈሱልኘ፡፡ ለጊዜው ሀገራችን ያሏትም ማኅበራዊ፤ሃይማኖታዊ፤ፖለቲካዊ የሆኑ መልካም እሴቶች በመጠቃቀስ እና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመጠቋቆም ለማስረዳት ብሞክርም እንዲህ ያለ የተሳሳተም ሆነ ተስፋ የመቁረጥ አመለካከት ያለውን አብዛኛውን ሕዝብ ሳስብ ችግሩ በትውልድ ደረጃ እንጂ እንዲህ በአንዴ ሊቀረፍ እንደማይችል ስረዳ ውስጤ የሚፈጠሩ ነገሮችን በማሰብ አዘነ፡፡ የሆነው ሆኖ በዚሁ ርዕስ ላይ ብዙ ውይይቶች አድርገን ለጊዜው መስማሚያ ሀሳብ ላይ ደረስን፡፡ ከዚህም አልፈን አርዕስቶቸችን በመቀየር የመውረጃ ቦታችን ደረሰ ወይስ አልደረሰ እስክንል ድረስ ብዙ ጉዳዮቸን ዳሰሰን፡፡ እንዲያውም በዝምታ ያሳለፍኳ ቸውን ጊዜያት በቁጭት አሰበብኳቸው፡፡ ለካ  በአጋጣሚው ሁሉ መነጋገገር ብዙ ቁም ነገር ያስገኛል!!!
                        የካቲት 10፣2003 ዓ.ም ፣ባሕርዳር

Sunday, December 26, 2010

የገና ዛፍ ለኢትዮጵያውን ተገቢ ነውን?

እኛ ኢትዮጵያውያን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰውና የአባቶቻችንን ህሊና አንቅቶ በቀመሩልን የዘመን አቆጣጠራችን መሰረት የጌታችንን ልደት በዓል መታሰቢያ የበዓሉን ምስጢር ከቤተ ክርስቲያናችን በተረዳንው መልኩ ወቅቱን ጠብቀን በየዓመቱ እናከብራለን፡፡ አከባበሩም ምስጢሩን የጠበቀ ሃይማኖታዊ ባህል አለው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ዛሬ ሳናውቀው ተለመደንና በቤታችን፣ በስጦታችን፣በፌስቡክ ፕሮፋይላችን ሁሉ የምዕራባውያንን ባህል ወርሰን ‘የገና ዛፍን’ ለበዓሉ መግለጫ እንጠቀምበታለን፡፡ለምዕራባውያን የገና ዛፍ እራሱን የቻለ ለጌታችን ልደት ግን ያልተገባ ታሪክ አለው፡፡ እስቲ ‘የገና ዛፍ’ ከጌታችን ልደት ጋር ምን አገናኘው? መጠቀማችንስ አግባብ ነው ትላላቸሁ?ብንወያይ?